ATW Engineering
#ATW_ኢንጅነሪንግ በ2007 የሽመና ማሽን በማምረት ስራውን የጀመረ ሲሆን ምርቱን በዓይነትና በመጠን እያሰፋና እያዘመነ በመምጣት አሁን ላይ ዲጅታል ቴክኖሎጅን የሚጠቀሙ ማሽኖችን ወደማምረት የተሸጋገረ ኢንተርፕራይዝ መሆኑን የኢንተርፕራይዙ መስራችና ስራ አስኪያጅ አቶ አይሸሽም ጥላሁን ተናግረዋል፡፡
#ATW_ኢንጅነሪንግ የተለያዩ አምራች ኢንተርኘራይዞችና ፋብሪካዎች የሚጠቀሙባቸውን ማሽኖችን እያመረተና እያቀረበ የሚገኝ ሲሆን 85 በመቶው የሚሆነውን ምርቱን የሚያመርተው በደንበኞች ትዕዛዝ፣ 15 በመቶው የሚሆነውን ደግሞ በምርምር እየሰራ ለገበያ እያዋለ ይገኛል።
ኢንተርፕራይዙ ምርቶቹን በአዲስ ካፒታል እና በዋሊያ ካፒታል ዕቃ ፋይናንስ በኩልም ለአምራች ኢንተርፕራይዞች እያቀረበ ይገኛል።
ከ15 በላይ ቋሚ ሰራተኞች ያሉት #ATW_ኢንጅነሪንግ የሀገር ውስጥ ጥሬ ዕቃን በመጠቀሞ ከዲዛይን አንስቶ ከግብዓት መረጣ እስከ ምርት ሂደት ድረስ ባሉት ባለሙያዎች ተኪ ምርትን መተካት የሚችሉ ማሽኖችን እያመረተ ይገኛል።